image
image
image
image
image

"ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር እና የሰራተኛውን እውቀት በአግባቡ በመጠቀም የተያዙ የልማት ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ ነው።"- ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ

ህዳር 8, 2017
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ለሰራተኛውና ለተገልጋዮች ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር የሚያስችሉ ደረጃቸውን የጠበቁ የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ስራ አስጀመረ። በዚህ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ አጠቃላይ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ዘላቂ እና ጠንካራ ተቋም ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። ወ/ሮ ልዕልቲ አክለው ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር እና የሰራተኛውን እውቀት በአግባቡ በመጠቀም የተያዙ የልማት ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። አስተዳደሩ፤ በላቀ ትጋትና ቁርጠኝነት ህዝብን በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ መሆኑን ያነሱት ወ/ሮ ልዕልቲ ሰራተኞች ደግሞ በታማኝነትና በቅንነት ህዝቡን እንዲያገለግሉ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን አስረድተዋል። የመንግስት ሰራተኞችን የኑሮ ጫናን ለማቃለል በመንግስት በኩል የተለያዩ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በስራው አከባቢ ያለአንዳች እንግልት አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችሉ ሰራተኛው አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች በቅረብ እንዲያገኝ ያስችላል ብለዋል። በዚህ መርሀ ግብር ላይ የአገልግሎት አሰጣጡን የበለጠ ለማሳለጥ የሚያስችሉ ደረጃቸውን የጠበቁ ቴክኖሎጅዎችን ስራ ማስጀመሩን ወ/ሮ ልእልቲ አያይዘው ገልፀዋል። በዛሬው ዕለት ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት ማዕከል፣ ሱፐር ማርኬት፣ የህፃናት መጫዎቻ ስፍራ፣ የመጀመሪያ ህክምና አገልግሎት መስጫ ማዕከል፣ ቤተ-መጽሃፍት እና ሌሎችንም አገልግሎቶች ስራ አስጀምሯል። በተያያዘ አስተዳደሩ ስታንዳርዱን የጠበቀ የወረፋ ማስጠበቂያ፣ የውስጥና የውጭ ካሜራ መቆጣጠሪያ ሴንተር፣ ዲስፕሌዮች፣ ዲጅታል ዙም ሚቲንግ፣ QR ኮድ ያለው የሰራተኞች ባጅና ሌሎችንም የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደ ተግባር አስገብቷል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች