image
image
image
image
image

'ከጂኦ-ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና': የባህር በርና የብሔራዊ ጥቅም ጉዳዮች ውይይት ተደረገ።

መስከረም 30, 2017
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች "ከጂኦ-ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና" በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ወቅታዊ ሀገራዊና ዓለም አቀፍ አጀንዳዎችን በማንሳት ሰፊ ውይይት አካሂደዋል። ውይይቱ ሀገራዊ ስኬቶችን በመገንዘብ እና ብሔራዊ ጥቅምን በማስከበር ላይ ያተኮረ ነበር። የመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳው የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዮዲት ሰሎሞን፣ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የሀገርን ከፍታ የሚያረጋግጡ በርካታ ስኬታማ ተግባራት ደረጃ በደረጃ እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል። ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ይህንን ታሪካዊ ወቅት ተገንዝቦ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል። ወ/ሮ ዮዲት አክለውም፣ በእድገት ጎዳና ላይ የምትገኘው ሀገራችን ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የተሰራውን ታሪክ፣ በባህር በር ጉዳይም ላይ መድገም እንደሚገባት አጽንኦት ሰጥተዋል። ይህንን ለማሳካት ሰራተኛው የስነ ልቦና የበላይነትን በመያዝ በብሔራዊ ጥቅም ላይ በጋራ መቆም እንዳለበት አስገንዝበዋል። የባህር በር ጉዳይ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ በሰላማዊ መንገድ መልስ እንዲያገኝ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፣ የመንግስት ሰራተኛው በቁጭት በጋራ መቆም እንደሚገባ አሳስበዋል። በመድረኩ ለውይይት መነሻ ሆኖ የቀረበው ሰነድ በብሔራዊ ጥቅምና በጂኦ-ስትራቴጂያዊ ቁመና ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን፣ ሀገራዊና ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን ዳስሷል። ሰነዱን ያቀረቡት የወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ደበላ ናቸው። የውይይት መድረኩን የመሩት የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ም/ፓርቲ ኃላፊና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳምጠው ወንታሞ ሲሆኑ፣ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሀገራዊ ስብራቶች በመጠገናቸው ኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል። አቶ ዳምጠው አክለውም፣ ትናንት አባቶቻችን ያስረከቡንን ታላቅ ሀገር ክብሯንና ታላቅነቷን በተጠበቀ መንገድ ለልጆቻችን እና ለሚመጣው ትውልድ ለማስረከብ በመንግስትና በህዝብ ርብርብ ወደ ቀደመ ሉዓላዊ ክብሯ እየተመለሰች መሆኑን አስገንዝበዋል። ውይይቱ ከተካሄደ በኋላ አስተያየት የሰጡ የመንግስት ሰራተኞች በበኩላቸው፣ እንደ መንግስት ሰራተኛ ውስጣዊ አንድነታችን በማጠናከር ጂኦ-ስትራቴጂያዊ ቁመናችን በመግናጸፍ ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር በጋራ እንቆማለን ሲሉ ገልጸዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች