የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት

  1. የተቋም አቅም ግንባታ ስራን የሚያሳልጡ ዘመናዊ አሰራሮችንና ተሞክሮዎችን በመለየት በክ/ከተማ አስተዳደሩ መስሪያ ቤቶች ላይ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ አስፈላጊዉን የቴክኒክና የሙያ ድጋፍ ይሰጣል፤

  2. በመንግስት መስሪያ ቤቶች የሰዉ ሀብት ልማት በቀጣይነት የሚለማበትንና ጥቅም ላይ የሚዉልበትን ስርዓት ይዘረጋል፤ ይተገብራል፤ እንዲተገበር ያደርጋል፤

  3. በክ/ከተማው አስተዳደር መስሪያ ቤቶች የሚሰጡ አገልግሎቶች ተገቢዉ ስታንዳርድ መኖሩን ያረጋግጣል፤ እንዲያዘጋጁ ያደርጋል፤ ያጸድቃል፤ ተግባራዊ መደረጉን ያረጋግጣል፤

  4. በከተማው አስተዳደር መስሪያ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ አፈጻፀም ይከታተላል፣ የተገልጋዩን እርካታ ጥናት ያካሂዳል፣ የጥናቱን ውጤት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤

  5. የመንግስት ሰራተኞች ቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለዉ መንገድ መዘርጋቱንና ተግባራዊ መደረጉን እንዲሁም ዉጤታማነቱን ያረጋግጣል፤

  6. ያልተማከለ የአስተዳደር ስርዓትን ለማጠናከር የሚያስችል የማስፈጸም አቅም ግንባታ ይዘረጋል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣ ይደግፋል፤

  7. የመንግስት ሰራተኞችን ወቅታዊ አፈፃፀም ምዘና የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ተግባራዊነቱንም ያረጋግጣል፤

  8. የመንግስት ሰራተኛ በብቃትና በአፈጻፀም ላይ የተመሰረተ የምደባ፣ የደረጃ ዕድገትና የእርከን ጭማሪ፣ የጥቅማጥቅምና የማበረታቻ ስርዓት ይዘረጋል፣ እንዲተገበር ያደርጋል፤ ውጤታማነቱን ይገመግማል፣ አስፈላጊዉን የማሻሻያ እርምጃ ይወስዳል፤

  9. የመንግስት ሰራተኞች አቀጣጠር፣ አመዳደብ፣ የደረጃ እድገት፣ ዝውውር፣ አበልና ጥቅማ ጥቅም፣ ስልጠናና የዲሲፕሊን አፈጻጸም በህግ መሰረት መፈጸሙን ይከታተላል ያረጋግጣል፤

  10. በህግ መሰረት የከተማ አስተዳደሩን የመንግስት ሰራተኞችን ከጡረታ ዕድሜ ክልል በላይ በአገልግሎት ላይ ለማቆየት በሚቀርብ ጥያቄ ተቀብሎ ዉሳኔ ይሰጣል ለሚመከታወ አካል ያቀርባል፤

  11. የክ/ከተማ አስተዳደሩን የሰዉ ሀብት መረጃዎችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ያደራጃል፤

  12. የህዝብ አገልጋይነት አስተሳሰብ ያለዉ አመራርና ፈጻሚ ይገነባል እንዲገነባ ይሰራል፣ የብቃት ማረጋገጫ ስርዓት ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣ ይደግፋል፤ ያረጋግጣል፤

  13. በሚዘረጋቸው አዳዲስ አሰራሮች፤ አደረጃጀቶችና ማኑዋሎች ዙሪያ አጫጭር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ይሰጣል፣ እንዲሰጥ ያደርጋል፤ ፣

  14. ሁሉም ተቋማት ዉጤታማ አፈጻፀም እንዲኖራቸዉ የሚያደርጋቸዉን አዳዲስ የለውጥ መሳሪያዎች ከራሳቸዉ ባህርይ አንጻር አጥንተው እንዲያቀርቡ ያበረታታል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፣፤

  15. የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ አፈጻጸም ውጤታማነት ይመራል፣ አፈጻጸማቸውን ይገመግማል፣ ግብረ- መልስ ይሰጣል፣ ደረጃ ያወጣል፣ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ይልካል፣

  16. ከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ላይ የሰራተኞች አፈጻጸም ምዘና ተግባራዊ እንዲሆን ሥርዓት ይዘረጋል፣ አፈጻጸሙን በመፈተሸ ግብረ-መልስ ይሰጣል፣ የምዘና ሂደቱ በበላይነት ያስተባብራል፣ ያረጋግጣል፡፡