በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር የሴቶችና ህጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት ፡-
- ለሴቶች የማህበራዊ አገልግሎት ድጋፍ መስጠት
- ከፍለው መማር ለማይችሉ ሴቶች የትምህር እድልና ድጋፍ ማመቻቸት
- ሴቶችን በገቢ ማስገኛ ዘርፎች እንዲሰማሩ ድጋፍ መስጠት
- ሴቶች የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው ማመቻት
- ሴቶች የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሁኔታዎችን ማመቻት
- ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መከላከልና ተግባራዊ ምላሽ መስጠት
- ለጥቃት ተጎጂዎች ተግባራዊ ምላሽ መስጠት : የህግ ምክር አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ
- አማራጪ የህፃናት እንክብካቤ (ጉድፍቻ ,አደራ ቤተሰብ ) አገልግሎት መስጠት
- ምክር ምክክርና አመራር አገልግሎት መስጠት
- ለህፃናት የስነ ልቦና አገልግሎት መስጠት
- ለህፃናት ቤተሰብ ምክር አገልግሎት መስጠት
- የአልሚ ምግቦችን ለእርጉዝ እናቶችና ጨቅላ ህፃናት አቅርቦት ክትትል
- ተጠቃሚዎችን ከመሰረታዊ ማህበራዊ አገልግሎት ማተሳሰር
- ለተጠቃሚዎች የኑሮ ማሻሻያ አገልግሎት መስጠት
- ለከፋ የማህበራዊ ችግር ውስጥ ለገቡ የህብረተሰብ ክፍሎች ማህበራዊ ድጋፍ ማድረግ
- ለእድሮች የምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት መስጠት
- ለአካል ጉዳተኞችና አረጋዊያን የተሃድሶ አገልግሎት መስጠት
- የሰው ሰራሽ አካልና አካል ድጋፍ አገልግሎት ማመቻት
- አቅም ለሌላቸው አካል ጉዳተኞችና አረጋውያን በነፃ ህክምና/የጤና መድህን አገልግሎት ማመቻቸት