የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የክ/ከተማችን ብሎም የወረዳችን ነዋሪ ፈጣን፣ ተደራሽ እና ጥራት ያለው አገልግሎት የማግኘት መብት ያለው በመሆኑ ይህንን የህዝባችንን ፋላጎት ዕውን ከማድረግ አኳያ የአገልገሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ዘመናዊ ማድረግ እንዲሁም ቀጣይነት ባለው መልኩ ራሱን እያሻሻለ እና እያሰደገ የሚሄድ በስነምግባሩ የተመሰገነ፣ ነፃ ገለልተኛ የሆነ ፐብሊክ ሰርቪስ መፍጠር ዋነኛው ጉዳይ ሊሆን ይገባል፡፡
የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው የሚገኙ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለዉጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በስነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰዉ ኃይል እንዲመራ የማድረግ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የህዝቡን የመገልገል መብቶች በተሟላ ሁኔታ በማስጠበቅ የዜጎች ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት እነሰራለን፡፡
አቶ ስንታየሁ ደበላ , የልደታ ወረዳ 6 ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ